ICT park በድሬ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ እንደሚሳተፍ አሳወቀ ::

2023-11-27
Event Image

አይሲቲ ፓርክ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከስካይሊንክ ቴክኖሎጂስና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ በሚያዘጋጁት ድሬ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ እንደሚሳተፍ አሳወቀ። ይህንን ያሳወቀው የስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ አመራሮች ከአይሲቲ ፓርክ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። ድሬ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በአሁኑ ጊዜ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ያሳወቁ ሲሆን አይሲቲ ፓርክም በሥሩ ካሉ ተቋማት ጋር የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዞ ይገባል። "1ኛው ዓለም አቀፍ ድሬ ኤክስፖ" ከጥር 15-19 በድሬዳዋ ከተማ idea to reality ከሃሳብ እስከ ትግበራ" በሚል መርህ የሚከናወን ይሆናል። ይህ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰማሩ አገር በቀል እና የውጭ ተቋማት በስፋት የሚሳተፉበት ከ40,000 ሺ በላይ ጎብኚዎች እንደሚጎበኙት እንደሆነ ተገልጿል።